ወሌ መሐመድ መስጂድ

ታሪክ

የመጀመሪያው የአዲስ አበባ ከተማ መስጂድ… አዋሬ ሰፈር… ከቤተመንግስት በስተምስራቅ ዝቅ ብሎ… ወሌ መሀመድ መስጂድ። ምኒሊክ ቤተ–መንግስትና ቤተ–ክርስተትያን (ግቢ ገብርኤል) ለማስገንባት ከውጭ ሀገር መሀንዲስ ያስፈልጋሉ። መሀንዲሱም በፍለጋ ለጊዜው በውል ካልታወቀ የእንግሊዝ ቅኝ ግዛት ስር ከነበረችው የሰሜን አፍሪካ ሀገር ይገኛል። መሀንዲሱም ወደሀገራችን ይመጣል… ስራውንም ይጀምራል… ሙስሊም በመሆኑ ነገር ግን የሚሰግድበት መስጂድ ስለሌለ ከሚሰራበት አጠገብ ሜዳ ላይ ይሰግዳል። ይህንን ሁኔታ (ሰላቱን) ያዩ የወቅቱ ሹማምንቶችና የክርስትና ሀይማኖት አባቶች የሚያሳፍር ድርጊት መሆኑን ይነጋገሩበታል። ሆኖም ግን መሀንዲሱን ወደሀገሩ እንዳይመልሱት ፖለቲካቸው ከመበላሸቱም በሻገር ለግንባታውም ሌላ መሀንዲስ መፈለጉ ጊዜ ማባከን በመሆኑ ከለላ አድርጎ በድብቅ እንዲሰግድ ቦታ ይሰጡታል። ከተወሰነ ጊዜ በኋላም ተደብቀው ይሰግዱ የነበሩ የመንደሩ ሙስሊሞች ከመሀንዲሱ ጋር በህብረት ሆነው መስገድ ጀመሩ። ቀስ በቀስም የመንደሩ ሙስሊሞች ኅብረት ሲጠነክር በየአመቱ በረመዳን ወር በየገጠሩ ያሉ አሊሞች ደረሶቸሰቸውን ይዘው በዚሁ መስጂድ ያሳልፉ ጀመር። ገጠመኙ የነቢዩ ሙሳን ታሪክ ያስታውሰናል… ኢስላም በሩቁ ሲጠላ ሲናቅ… በአጠገባቸው በቤተ–መነረግስቱ ስር ፍሬው ተተከለ ቡቃያው በቀለ አበባው አፈራ።

አጭር መግለጫ

  • መገኛ : የካ ክ/ከተማ
  • የሰፈሩ ልዩ ስም: አዋሬ
  • የተመሰረተበት ዘመን: 1898
  • ስፋት በካ.ሜ: 848
  • የጁመአ ሰላት: ይሰገዳል
  • ይዞታ: የመንግስት
  • ካርታ: አለው
  • የሴቶች ቦታ : አለው
  • መድረሳ: አለው
  • መፀዳጃ ቤት: አለው
  • የውዱእ ቦታ: አለው
  • ሻወር: አለው
  • የመኪና ማቆሚያ: የለውም

አድራሻ

ፕሮገራሞች

እለታዊ
ሳምንታዊ
ወርሀዊ

ፎቶ

Social Media
 
 
 
  

Leave a Reply