አንዋር መስጂድ

ታሪክ

አንዋር መስጂድ ከተሰራ በኋላ ለህንፃ ተቋራጩ የሚከፈል ገንዘብ ጠፍቶ መስጂዱ
ተከሷል። ፍርድ ቤትም መስጂዱ እንዲዘጋ ወስኗል። በአንዋር መስጊድ ኮሚቴ ‹‹ታላቁ የአንዋር መስጊድ በአዲስ አበባ›› በሚል ርዕስ
በራስ ተፈሪ (ኃይለሥላሴ) ውድቀት ማግስት የተጻፈው መጽሐፍ እንዲህ ይገልጻል፡–

#‹‹መስጊዱ አል-አንዋር ተሰርቶ እንዳለቀና ለጸሎት አገልግሎት ከዋለ በኋላ የሕንፃው ሥራ ተቋራጭ መስጊዱን ሰርቶ ሲያስረክብ ቀሪ የነበረው የ16.000 (አሥራ ስድስት ሺህ ብር) ሒሳብ ስላልተከፈለና የተወሰነ የጊዜ ገደብ ስላለፈ ከፍርድ ቤት በመጣው ትዕዛዝ መሠረት መስጊዱ እንዲዘጋ አድርጎት ነበር።

#ምንም እንኳን ነዝሩ በዚያን ጊዜ መስጊዱ ምንም ገንዘብ የሌለው መሆኑን ለሥራ ተቋራጩ ቢያስገነዝብም መጠነኛ ጊዜ እንኳ ለመስጠት ተቋራጩ ሳይፈቅድ ቀረ። ከዚህ በኋላ
የመስጊዱ አስተዳዳሪ የእስልምና ሃይማኖት ተከታይ የሆኑ አዛውንቶችና ሽማግሌዎች ተሰብስበው ምክር ካደረጉ በኋላ ይህ በፍርድ የተወሰነብን ገንዘብ ከምንም ይምጣ ከምን በ24 ሰዓት ውስጥ እንዲከፈል ተወሰነ። ቢሆንም ይህ ገንዘብ በዚህ ሰዓት ውስጥ ባይከፈል ደግሞ ከመስጊዱ መሬት ቀንሰው በሀራጅ እንዲሸጥ፣ ለተቋራጩ የሚከፈል
መሆኑን ፍርድ ቤቱ በተጨማሪ አሳሰበ።››

#የሆነው ሆኖ የአንዋር ናዝር የነበሩት ሐጂ አቡበከር ሸሪፍ አስቸኳይ ስብሰባ ጠርተው ሙስሊሙን አወያዩ። የሙስሊሙ ዓይን የነበረው ታላቁ የአንዋር መስጂድ ከሚዘጋ በሚል ሙስሊሙ ያለውን ሁሉ አወጣ።ተሳክቶም የአንዋር መስጊድ 16 ሺህ ብሩን ከሙስሊሙ ተበደረ።

#ብድሩን የሰጡት
ሐጂ ራህመቶ ሙክታር (5 ሺህ)
ሐጂ አብዶ አርሲ (2 ሺህ)
ሐጂ ዑመር ኢብራሂም (1ሺህ)፣
ሐጂ ሙዘይን ኡስማን (1 ሺህ)፣
ሐጂ አቡበከር ሸሪፍ (2 ሺህ)፣
ሐጂ ሙሐመድ ጀማል (3 ሺህ)፣
ሐጂ ጀማል ሐሰን (1 ሺህ) እና
ሐጂ በሽር ገዳ (1 ሺህ) ነበሩ። አላህ ይቀበላቸው

አጭር መግለጫ

 • መገኛ: አዲስ ከተማ ክ/ከተማ
 • የሰፈሩ ልዩ ስም: መርካቶ
 • የተመሰረተበት ዘመን: 1933
 • ስፋት በካ.ሜ: 20,687
 • የጁመአ ሰላት: ይሰገዳል
 • ይዞታ: የመንግስት
 • ካርታ: አለው
 • የሴቶች ቦታ : አለው
 • መድረሳ: አለው
 • መፀዳጃ ቤት: አለው
 • የውዱእ ቦታ: አለው
 • ሻወር:
 • የመኪና ማቆሚያ:

አድራሻ

ፕሮገራሞች

እለታዊ
ሳምንታዊ
ወርሀዊ

ፎቶ

Social Media
 
 
 
  

Leave a Reply