አማን አምባ መስጂድ

ታሪክ

ሰፈሩ ቀጨኔ መድሀኒአለም ይባላል። በተለምዶ ኢትዮጵያ የክርስቲያን ደሴት ናት እንደሚባለው ሁሉ ቀጨኔም በአዲስ አበባ የክርስትያን ደሴት ትባል ነበር። አሁን አሁን ቀረ እንጂ በቀደምት ስርአቶች እንዃን መስጂድ ሊሰራ ይቅርና አንድ ሙስሊም ኮፊያ አድርጎ በዚያ አካባቢ እንደማያልፍ ለአዲስ አበባ ሙስሊሞች የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነው። ወቅቱ የኢህአዴግ ዘመን ነው ሀጅ መሀመድ አወል ረጃ ለአካባቢው ሙስሊም ነዋሪዎች ለረመዳን ፆም ማፍጠሪያ እንዲሆናቸው ዘንድ አንድ በሬ ይሰጧቸዋል። ሙስሊሙም ማህበረሰብ ያሉበትን አካባቢ ጠንቅቀው ስለሚያውቁ አብረን ከምንኖር ወገኖቻችን እንዳንጋጭ እንዳንቀያየም ይህን በሬ ከከተማው ወጣ አድርገን እንረደው ይባባሉና ወደ ተራራው ወጣ ብለው ያርዳሉ። እዚያም ቢሆን ነገሩ አልቀረላቸውም። “የጠሉት ይወርሳል የፈሩት ይደርሳል” እንዲሉ እዚያም ተከትሏቸው ይመጡና “መሬታችንን ልታረክሱ ሰፈራችንን ልታበላሹ …” በሚል ውዥንብር ኃይለኛ ፀብ ይፈጠራል። በተከሰተውም ግጭት ሙስሊሙ ብሶቱ ይገነፍላል: ቁጭቱ ይቀሰቀሳል: እልሁ ይገፋፋዋል… ሆኖም ግን ሁኔታውን በትእግስት ያሳልፍና በህብረት በመሆን ጉዳዩ ወደሚመለከተው የመንግስት አካል ማመልከቻ ያስገባሉ። መንግስትም በሬው የታረደበትን ቦታ ለአካባቢው ሙስሊም ነዋሪዎች ለቀብር አገልግሎት ሰጠ። በጎኑም አማን አምባ የሚባል መስጂድ ተሰራ ። ባልታሰበ ሁኔታ ባልታቀደ ቦታ በ1990 መስጂዱ ተቆረቆረ።

አጭር መግለጫ

  • መገኛ: ጉለሌ ክ/ከተማ 
  • የሰፈሩ ልዩ ስም: ቀጨኔ መቀበያ
  • የተመሰረተበት ዘመን: 1990
  • ስፋት በካ.ሜ: ከቀብር ጋር
  • የጁመአ ሰላት: ይሰገዳል 
  • ይዞታ: የመንግስት
  • ካርታ: አለው 
  • የሴቶች ቦታ : አለው
  • መድረሳ: አለው
  • መፀዳጃ ቤት: አለው
  • የውዱእ ቦታ: አለው
  • ሻወር:
  • የመኪና ማቆሚያ:

አድራሻ

ፕሮገራሞች

እለታዊ
ሳምንታዊ
ወርሀዊ

ፎቶ

Social Media
 
 
 
  

Leave a Reply