ጃዕፈር መስጂድ

ታሪክ

የ350 ብር ታሪክ ነው ጉደዩ፣ ቦሌ ሩዋንዳ ተብሎ በሚጠራው መንደር ውስጥ ለረጅም ጊዜ ሙስሊሞች የመስገጃ ቦታ አጥተው ይንከራተቱ ነበር፡፡ በወቅቱም በአካባቢያቸው ለምንም ጥቅም ያልዋለ ሰፊ ቦታ ነበር፡፡ ሙሰሊሙም መሄጃ ሲያጣና ትግስቱ ተሟጦ ሲያልቅ ይህንን ባዶ መሬት በማግኘታቸው ለመስገጃነት መጠቀም ጀመሩ፡፡ በክረምት ወቅት ቦታው ጭቃ ሆኖ ለሰላት ስላስቸገራቸው የሚነጠፍ ድንጋይ ያስመጣሉ፡፡ ቀበሌውም ህገወጥ ነው በማለት የተራገፈውን ድንጋይ በመኪና አስጭኖ ያስወስደዋል፡፡ በቦታውም እንዳይሰገድ የከለክላል… ሙስሊሙም ማህበረሰብ ማመልከቻቸውን ይዘው ወደሚመለከተው የበላይ አካል ይሄዳሉ… ቀበሌውም ጉዳዩ ሳይታይላችሁ በፈት ድንጋዩን ያስጫንበትን እንድትከፍሉ በማለት ነዋሪው ሙስሊም 350 ብር እንዲከፍል ይወሰንበታል፡፡ ህብረተሰቡም ገንዘቡን አዋጥተው ከፈሉ… ሂደቱም ቀጠለ ታሪክ ላይ ሰፍሮ… እዚያው ቦታ ላይ በ 11000 ካ.ሜ. ላይ በ 1988 ጃእፈር መስጂድ ተቆረቆረ፡፡

አጭር መግለጫ

 • መገኛ: ቦሌ ክ/ከተማ 
 • የሰፈሩ ልዩ ስም: ሩዋንዳ  
 • የተመሰረተበት ዘመን: 1988
 • ስፋት በካ.ሜ: 12646
 • የጁመአ ሰላት: ይሰገዳል
 • ይዞታ: የመንግስት
 • ካርታ: 
 • የሴቶች ቦታ : አለው
 • መድረሳ: አለው
 • መፀዳጃ ቤት: አለው
 • የውዱእ ቦታ: አለው
 • ሻወር: አለው
 • የመኪና ማቆሚያ: አለው

አድራሻ

ፕሮገራሞች

እለታዊ
ሳምንታዊ
ወርሀዊ

ፎቶ

Social Media
 
 
 
  

Leave a Reply