ዑመር ኢብኑል ኸጣብ መስጂድ

ታሪክ

አቃቂ በሰቃ ነው ቦታው ወደ ደብረዘይት ሲኬድ መሿለኪያ ድልድይ አለፍ እንደተባለ በስተግራ በኩል ለጥ ያለ ሜዳ ላይ ግርማ ሞገስ ያለው መስጂድ በአወሊያ በኩል በተገኘ እርዳታ ተሰርቶ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል። በዲሞክራሲው ብርሀን ለቃሊቲ፣ ለአቃቂና ለአካባቢያቸው ሙስሊም ነዋሪዎች ለኢድ ሰላት መስገጃነት በመንግስት በኩል የተሰጠ ቦታ ነው። ሆኖም ግን በመስጂድ እጦት ሲንከራተት የነበረው የአካባቢው ሙስሊም ማህበረሰብ “በአመት ሁለት ጊዜ ብቻ ከምንሰግድበት ለምን በቀን አምስቴ አንሰግድበትም ” በማለት ውይይት ያደርጋሉ። ማመልከቻም ይዘው ጉዳዩ ወደሚመለከተው የመንግስት አካል ይሄዳሉ። ከታች ያሉት ባለስልጣናትም አቤቱታው ተቀባይነት የለውም በማለት ቁጣና ዛቻ አዘል መልስ ይሰጧቸዋል። የአካባቢው ሙስሊሞች የተሰጣቸውን የንቀትና የጥላቻ መልስ ወደጎን በመተው ትግላቸውን ቀጠሉ… ወደ በላይ አካል… የበላይ አካልም ዘችግሩን በማጥናትና መንግስት ለሙስሊሙ ያጎናፀፈውን መብት መሰረት በማድረግ የ20,000 ካሬ ሜትር ቦታ ሰጣቸው። ይህ ፍትሀዊ አሰራር ያንገበገባቸው የመንግስት ወንበር ለወጥመድነት የሚጠቀሙ ግለሰቦች “አስፋልት ፊትለፊት ስለማይገባችሁ አይሰጣችሁምና ወደውስጥ ገባ በሉ ” በማለት ጥላቻቸውን በመግለፅ ሂደቱ እንዳይሳካ ያላደረጉት ጥረት ያልፈነቀሉት ድንጋይ አልነበረም። ሆኖም ግን የሚሳካው የሰዎች ሀሳብ፣ ፍላጎትና ስሜት ሳይሆን የአላህ (ሱ·ወ·) ውሳኔ ነውና አስፋልቱ ዳር ኡመረደ ኢብኑል ኸጣብ መስጂድ ተመሰረተ… በ1988።

አጭር መግለጫ

 • መገኛ: አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ 
 • የሰፈሩ ልዩ ስም: አቃቂ መሻለኪያ
 • የተመሰረተበት ዘመን: 1988
 • ስፋት በካ.ሜ: 20000
 • የጁመአ ሰላት: ይሰገዳል 
 • ይዞታ: የመንግስት
 • ካርታ: አለው 
 • የሴቶች ቦታ : አለው
 • መድረሳ: አለው
 • መፀዳጃ ቤት: አለው
 • የውዱእ ቦታ: አለው
 • ሻወር:
 • የመኪና ማቆሚያ:

አድራሻ

ፕሮገራሞች

እለታዊ
ሳምንታዊ
ወርሀዊ

ፎቶ

Social Media
 
 
 
  

Leave a Reply