ኑር አምባ መስጂድ

ታሪክ

የካባ ድንጋይ የሚወጣበት አካባቢ ነው ቦታው፡ ገደል አፋፍ፡፡ በቀለበት መንገድ ከአየርጤና ወደ  ቃሊቲ በሚወስደው መንገድ በሀናማሪያም መሿለኪያ ድልድይ ወደ ቀኝ በግምት ከ3-4 ኪ.ሜ. ገባ ብሎ ሁለት ጓደኛሞች በ500 ካ.ሜ. ላይ የጋራ ወፍጮ ቤት ይከፍታሉ፡፡ ከጊዜ በኋላም ሁለቱ ጓደኛሞች ይጣላሉ፡፡ ንብረቱን ለመከፋፈል ይስማማሉ፡፡ ከሁለቱ ሰዎች የአንደኛው ወንድም ወፍጮ ቤቱን ይገዛቸዋል፡፡ ከዚያም የአካባቢው ሙስሊም ማህበረሰብ እንዲሰግድበት ወደ መስጂድ ቀይሮ ወቅፍ ሰጠ፡፡ በ 1996 ወፍጮ ቤቱ ወደ ኑር አምባ መስጂድ ተለወጠ፡፡ የሁለት ሙስሊም ወንድማማቾች መጣላት ወፍጮ ቤቱን ወደ አላህ ቤት ቀየረው፡፡ መጥፎ መስሎ የመጣውን ነገር አላህ (ሱ.ወ.) ወደ መልካም ሊለውጠው እንደሚችል የቁርአንን አንቀፅ (ሱረቱል በቀራ 216) ያስታውሰናል፡፡

አጭር መግለጫ

 • መገኛ: ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ 
 • የሰፈሩ ልዩ ስም: ሃና ማርያም ካባ
 • የተመሰረተበት ዘመን: 1996 
 • ስፋት በካ.ሜ: 500
 • የጁመአ ሰላት: ይሰገዳል 
 • ይዞታ: የግለሰብ
 • ካርታ: የለውም
 • የሴቶች ቦታ : አለው
 • መድረሳ: አለው
 • መፀዳጃ ቤት: አለው
 • የውዱእ ቦታ: አለው
 • ሻወር:
 • የመኪና ማቆሚያ:

አድራሻ

ፕሮገራሞች

እለታዊ
ሳምንታዊ
ወርሀዊ

ፎቶ

Social Media
 
 
 
  

Leave a Reply